የጉባኤው ስብሳቢ
ሥልጣንና ተግባር
አባላት
ህጋዊ መሠረቶች
አዋጅ
የስነስርዓት ደንብ
ጉዳዮች 
ውሳኔ ያገኙ
በሂደት ላይ ያሉ
 
ህትመቶች
ፎርሞች
ዜና
ጨረታ
ማስታወቂያ
መልስ
የፎቶ ማህደር
ጠቃሚ አድራሻዎች
   
ሥልጣንና ተግባር  
   
 

አጣሪ ጉባኤው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፤

1.       አጣሪ ጉባዔው ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዬችን በማጣራት ሕገ መንግሥቱን መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል፡፡

2.       በፌዴራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጐች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሣ እና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሣኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፡፡

3.       በፍርድ ቤቶች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ፣

 

ሀ/ ሕገ መንግሥቱን መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርዱ ቤት ይመልሳል፤

ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሣኔ ያቀርባል፡፡