የተከበሩ አቶ ደግፌ ቡላ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ
አቶ ደግፌ ቡላ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑንሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመሆን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንዲያገለግሉ ተመርጠው ሥራ የጀመሩት ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም ነው።
የተከበሩ አፈ ጉባኤ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ከመምጣታቸውም በፊት ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባል በመሆን ላለፉት 3 ዓመታት አገልግለዋል።
አቶ ደግፌ ከመስከረም 1
ቀን 1997 እስከ መስከረም 25
ቀን 1998 ዓ.ም የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትህና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ከመስራታቸውም በላይ ከጥር 21 ቀን 1994 እስከ ነሐሴ 1996 የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት የአስተዳደርና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም ከጥቅምት 18
ቀን 1994 እስከ ጥር 21ቀን 1994
ዓ.ም የኦሮምያ የፍትህ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ በመሆን ኃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል።
አቶ ደግፌ ወደ ኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ከመመደባቸው ቀደም ሲልም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት ከየካቲት 1
ቀን 1990 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 1994 የኦሮምኛ ቋንቋ የቴሊቪዥን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኃላፊ ከሐምሌ 1 ቀን 1986 እስከ ጥር 30 ቀን 1990
ዓ.ም የኦሮምኛ ቋንቋ የቴሌቪዥንብ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ቡድን መሪ፣ ከሐምሌ 1 ቀን 1983 እስከ ሰኔ 30 ቀን 1986
ዓ.ም የኦሮምኛ ቋንቋ የቴሌቪዥን ክፍል ኃላፊ በመሆን ሲሰሩ ቆይተዋል።
በ1960 በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ፣ በኖሌ ካባ ወረዳ የተወለዱት
አቶ ደግፌ ከኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በህግ ትምህርት የLLB ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት በመጡ ባለሙያዎች በተሰጡ የአጫጭር ጊዜያት የሥልጠና ፕሮግራሞች በመሳተፍ በከፍተኛ የኃላፊዎች የአስተዳደር ስልጠና (Hight
Level Managment)፣ በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነትና በቴሌቪዥን ፕሮዳክሽንና ቴክኒክ የተለያዩ ሰርተፌኬቶች አግኝተዋል። |