ታሪክ
አወቃቀር
አፈ-ጉባኤዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ሥልጣንና ተግባር
ህጋዊ መሠረቶች
ህግ መንግስት
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 251/1993
የስብሰባና የስነስራት ደንብ
ሌሎች
ቋሚ ኮሚቴዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች 
ህገመንግስታዊ ትርጉም 
የህገመንግስትና የክልል ጉዳዮች
የገቢዮችና ድጎማ ጉዳዮች
ሌሎች
በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች
ስትራቴግክ እቅድ
ቃለ-ጉባኤ
ሪፖርት
ህትመቶች
ፎርሞች
ዜና
ጨረታ
ማስታወቂያ
መልስ
የፎቶ ማህደር
ጠቃሚ አድራሻዎች
ዜና

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአምስት ዓመት መርሐ ግብር ነድፎ

 እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ

የብሔር ብሔረሰቦችን ባህል የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽን ተከፈተ

          የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገመንግሠቱ የተሰጡትን ኃላፊነቶችና ተግባሮች በብቃት ለመወጣት ሚያስችል የአምስት ዓመት መርሐ ግብር ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስታወቁ፡ የኢትዮጵያ በሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ባህል የሚያንጽባርቅና የሚያስተዋውቅ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን በምክር ቤቱ ተከፈተ፡፡

አፈ-ጉባኤ ደግፌ ቡላ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን አቅም ለማጐልበት በምክር ቤቱ አዳራሽ ትናንት ለግማሽ ቀን በተካሄደው ውይይት መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ኃላፊነቶችና ተግባሮች በብቃት ለመወጣት እንዱያስችለው ከተያዙት ተግባራት አንዱ የአባላቱን አቅም ማጐልበት መሆኑንና ውይይቱም የዚሁ አካል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ምክር ቤቱ የተነደፈውን የአምስት ዓመቱን መርሐ ግብር ዛሬ በሚያካሂደው የምክር ቤቱ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅርቦ ለማጽደቅ መዘጋጀቱን ገልጽዋል፡፡

          ያምክር ቤቱን አባላት አቅም ለማጐልበት ለግማሽ ቀን የተካሄደው     ውይይት ዓለማ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ኃላፊነትና ተግባር ዙሪያ እንዲሁም   የፌዴራሊዝም ሥርዓቱን የበለጠ ለማጠናከር በሚያግዝ መልኩ ለምክር ቤቱ    አባላት ጠቃሚ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን አፈ-ጉባኤው አስረድተዋል፡፡    ውይይቱ  የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተሞክሮን ባካተተ የፌዴራሊዝም ጽንስ   ሃሳብ ላይ ያተኮረ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

                   ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማጠናከር የሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ለማድረግና የተጀመሩ ተግባራትን ከግብ ለማድረስ የምክር ቤቱ አባላት ከአባልነታቸው በተጨማሪ በተመደቡበት የሥራ መስክ የተጣለባቸውን ድርብ ኃላፊነት በትጋት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

          ዶክተር ፋሲል ናሆም የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪና የፍትሕና የሕግ ሥርዓት መመሪያ ዳይሬክተር #የፌዴራሊዝም ጽንሰ ሃሳቦችና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት$ በሚል ርዕስ ለውይይቱ ተከፋዮች ባቀረቡት ጽሑፍ ፌዴራሊዝም በይፋ መውጣት ከጀመረ ከሁለት መቶ ዓመት እንደማይበልጠው ጠቁመው፣ በዚህ አጭር ጊዜ ታዳጊ ሀገሮችን ጨምሮ በዓለም ካሉ መንግሥታት አብዛኞቹ የፌዴራል ሥርዓት ተከታይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

          ለእርስ በርስ ጦርነት ለተጋለጡና በአንድ ሥርዓት  ውስጥ ለማኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሰላም ተፈቃቅረው ለመኖር የፌዴራሊዝም ሥርዓት  ጥሩ መፍትሔ መሆኑ እንደታመነበት ዶክተር ፋሲል ገልጽው ፌዴራሊዝም በትክክል ተግባራዊ በሆነባቸው ሀገሮች አመርቂ ውጤት መገኘቱን አመልክተዋል፡፡

          ኢትዮጵያም በሕዝቦች እኩልነት ላይ የተመሠረተ ብሔረሰብአዊ ፌዴራሊዝም ሥርዓት እንደምታካሂድ ጠቁመው በሕዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሠረት አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ ለመገንባት በብሔረሰብ በጋራ ለመገንባት በብሔረሰባዊ መርህ ላይ የተመሠረተ ፌዴራል ሥርዓት ማዋቀሩ እንደትክክለኛ ምርጫ መወሰዱን በጽሑፋቸው ገልጽዋል፡፡

          በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገገው ብሔረሰባዊ ፌዴራሊዝም የሕዝቦች፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የጾታና የሰብአዊ መብቶች እኩልነቶችን ማረጋገጡን ጠቅሰው፤ ዓላማውም ዴሞክራሲን ለማስፈንና ልማትን ለማፋጠን መሆኑን አመልክተዋል፡፡

          ዶክተር ፋሲል በጽሑፋቸው ማጠቃለያ ዘመናዊ ፌዴራሊዝም በሰው ልጅ ታሪክ አዲስ ዓይነት የመንግሥት አወቃቀር በርካታ መንግሥታት የሚጠቀሙበት መንግሥታዊ አሰራር መሆኑን አስረድተው አንድን መንግሥት ፌዴራል የሚያሰኘው ሕገ መንግስታዊ የሥልጣን ክፍፍል ሲኖር አንደሆነም ገልጸዋል፡፡

          አቶ አየለ ውሉጌታ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ ዲን #የፊሲካል ዲሴንትራላይዜሽን ልምድ በኢትዮጵያ$ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ በኢትዮጵያ የፋሲካል ዲሴንትራላይዜሽን ሥርዓት እ.አ.አ በ2001 በአማራ፣ በኦሮሚያ፣በደቡብና ትግሪይ ወደ ወረዳ መውረዱንና በሌሎችም ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ በመስፋፋት ላይ መሆኑን ገልጽዋል፡፡

          በአዋጅ ቁጥር 33/1984 በፌዴራል መንግሥትና በብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮች መካከል ሊኖር የሚገባው የገቢ ምንጭ ክፍፍል መደንገጉን አቶ አየለ ጠቅሰው ከነዚህ ውስጥም የፌዴራልና ብሔሪዊ ክልላዊ መንግሥታት በተቀላጠፈ ሁኔታ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችሉ፣ ክልሎች በተነሳሽነት እራሳቸን እንዲያሳድጉ ማድረግ እንዲሁም በክልሎች መካከል ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ልዩነት ለማጥበብና የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ሥራዎች ለማበርታታት የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል፡፡

          በሌላ በኩልም በፌዴሬሽነ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ባህል የሚያንጸባርቅና የሚያስተዋውቅ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

          በኤግዚቢሽኒ መክፈቻ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዶክተር መሐመድ ሰርሃዬ ባደረጉት ንግግር፤የኤግዚቢሽኑ ዓላማ አንዱ የሌላውን ባህልና የአኗኗር ሥርዓት እንዱገነዘብና እንዲያውቅ በማድረግና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

          ምክር ቤቱ በሕዝቦች እኩልነትና መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር የማድረግ ኃላፊነት እንዳለው ዶክተር መሐመድ ጠቁመው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በታሪክ ሂደት ያፈራቸውንና ያካበቷቸውን የጋራ እሴቶች በማዳበር ከታሪካቸው የወረሷቸውንና የተዛቡ ግንኙነቶች በማረም ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የሚያስችሉ መድርኮችን መፍጠር ለምክር ቤቱ እነደሚጠቅም ገልጽዋል፡፡

          የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ የራሱን ባህል የመግለጽ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ  መብቱን ማስከበር የእያንዳንዱ ኃላፊነት ቢሆንም የዚህ  ያጋራ ተቋም የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የጋራ መድረኮችን የመፈጠርና የማመቻቸት ኃላፊነት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

          በኤግዚቢሽኑ ላይ 92 ፎቶግራፎች የቀረቡ ሲሆኑ ከነዚህ መካከልም 77ቱ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ በሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ገጽታ የሚያሳይና 15ቱ ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን የአሥር ዓመታት የሥራ ሂደት የሚገልጹ መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡

          እግዚቢሽኑን የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ ደግፌ ቡላ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ መርቀው የከፈቱ ሲሆን የየምክር ቤቶቹ አባላት ኤግዚቢሽኑን ጐብኝተዋል፡፡