የፌዴሬሽን
ም/ቤት ምክትል አፈ
ጉባኤ
የጀርመን
ልዑካን ቡድንን
አነጋገሩ
የፌዴሬሽን
ምክር ቤት ምክትል
አፈ ጉባኤ ዶክተር
መሐመድ ሰርሃዬ
በጀርመን የኢኮኖሚ
ልማት ትብብር ሚኒስቴር
የሚመራውን የልዑካን
ቡድን ተቀብለው
ሰኔ 9 1998ዓ.ም.
አነጋገሩ፡፡
የጀርመን
የኢኮኖሚ ልማት
ትብብር ሚኒስትር
ኤሪክ ስታተር በውይይቱ
ወቅት እንዳሉት፤
የጀርመን የልማት
ትብብር ከፌዴሬሽን
ምክር ቤት ጋር በልማት
አጀንዳዎች ላይ
ተባብሮ ለመሥራት
ከፍተኛ ፍላጐት
እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በጀርመንና
በኢትዮጵያ መካከል
በተለያዩ መስኮች
ለመተባበር የተለያዩ
ስምምነቶች በከፍተኛ
የመንግሥት ባለሥልጣናት
መካከል መፈረማቸውንና
ወደ ፊትም ከፌዴሬሽን
ምክር ቤት ጋር ሰፊ
የልምድ ልውውጥ
ለማድረግ መታሰቡን
ገልጸዋል፡፡
የፌዴሬሽን
ምክር ቤት ምክትል
አፈ ጉባዔ ዶክተር
መሐመድ ሰርሃዬ
ለልዑካን ቡድኑ
ስለ ጋራ በጅት አመዳደብ፣
በሃገሪቱ ውስጥ
ስላለው የህገ መንግስት ትርጉም
አተረጓጎም ስርዓት
እንዲሁም በኢትዮጵያ
እየተካሄዱ ስላሉት
የዲሞክራሲና የልማት
ግንባታዎች ሰፊ
ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ
ከቅርብ ጊዜያት
ወዲህ በዲሞክራሲ
ግንባታ ረገድ እያሳየች
የመጣችው አዎንታዊ
እድገት ወደ ፊትም
ተጠናክሮ እንደሚቀጥል
አስታወቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ
እየታዩ የመጡት
የልማትና የኢኮኖሚ
ዕድገቶች በአገሪቱ
የተጀመሩ የዴሞክራሲ
ግንባታ ሂደት ውጤቶች
እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ የመንግሥት
አወቃቀር መሠረት
ፌዴራል መንግሥቱ
በክልሎች ጉዳይ
ጣልቃ እንደማይገባና
ክልሎች የራሳቸውን
መብት የመወሰን
ህገ መግሥታዊ መብት
እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡
ወደ
ፊትም በጀርመንና
በኢትዮጵያ የፌዴሬሽን
ምክር ቤቶች መካከል
በሚደረጉ ግንኙነቶች
የፌዴሬሽን ምክር
ቤት ከጀርመን አቻው
ብዙ ጠቃሚ ልምዶችን
እንደሚቀስም እምነታቸውን
ገልጸዋል፡፡
|