ታሪክ
አወቃቀር
አፈ-ጉባኤዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ሥልጣንና ተግባር
ህጋዊ መሠረቶች
ህግ መንግስት
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 251/1993
የስብሰባና የስነስራት ደንብ
ሌሎች
ቋሚ ኮሚቴዎች
አባላት
የስነምግባር ደንብ
ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች 
ህገመንግስታዊ ትርጉም 
የህገመንግስትና የክልል ጉዳዮች
የገቢዮችና ድጎማ ጉዳዮች
ሌሎች
በሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮች
ስትራቴግክ እቅድ
ቃለ-ጉባኤ
ሪፖርት
ህትመቶች
ፎርሞች
ዜና
ጨረታ
ማስታወቂያ
መልስ
የፎቶ ማህደር
ጠቃሚ አድራሻዎች
    ዜና  
           

«የግንቦት ሃያ በዓል ብሔር ብሔረሰቦችንና ህዝቦችን በአንድነት ያስተሳሰረ ዕለት ነው»

                                                                                                                                 አፈ-ጉባኤ ደግፌ ቡላ

አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- የግንቦት ሃያ በዓል ብሔር ብሔረሰቦችን በአንድነት ያስተሳሰረ ዕለት መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ገለጹ፡፡

አፈ ጉባዔ ደግፌ ቡላ ኢትዮጵያ ቱዴ ከተባለ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የግንቦት ሃያ  የድል በዓል በኢትዮጵያውያን ህሊና ዘወትር ሲታወስ የሚኖር ታሪካዊ ዕለት ነው ብለውል፡፡

በአሉ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነትና የዜጎችን መብት ያረጋገጠ ከመሆኑም ባሻገር በአገሪቱ ዘላቁ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ወሳኝ ድርሻ ያበረከተ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

አፈጉባዔ ደግፌ ቡላ እንዳሉት ከግንቦት ሃያ የድል በአል በኋላ በአገሪቱ የተንሰራፋውን ድህነት ለመዋጋት መንግሥት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ መንቀሳቀሱን አመልክተው፣ በድህነት ቅነሳው ስትራቴጂም የተገኘው ተስፋ ሰጪ የኢኮኖሚ እድገት ብሔር ብሔረሰቦችን ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

ይህም የግንቦት ሃያ ድል አንዱ ውጤት እንደሆነና ብሔር ብሔረሰቦች ከደርግ አምባገነናዊ የአገዛዝ ሰንሰለት ነጻ የወጡበት ዕለት በመሆኑ ነጻነት ወዳድ ሕዝቦች በደማቅ ሁኔታ የሚያከብሩት እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

የግንቦት ወር ብሔር ብሔረሰቦችን ከጨቋኙ የደርግ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በተደረገው እንቅስቃሴ የማይዘነጋ ታሪካዊ ዕለት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥቱ አንድ አካልና ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚወከሉበት ተቋም መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሕገ መንግሥቱ በሰጠው ሥልጣን መሰረትም ሕገ መንግሥቱን ማስጠበቅ፣በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን መሸምገል፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና የክልሎችን ዓመታዊ በጀት ቀመር መሥራት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሴቶች ውክልና ባለፉት ጊዜያት ስምንት ብቻ እንደነበረ ያስታወሱት አፈ ጉባዔው፤ አሁን ካለው 112 መቀመጫ ውስጥ 21 የሚሆነው በሴቶች መያዙን አስታውቀዋል፡፡

የክልሎችን የበጀት ቀመርን በሚመለከትም ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ዓመታዊ በጀታቸውን የሚያገኙት ከፌዴራሉ መንግሥት መሆኑን ጠቁመው፤ ቀሪው የሚሸፈነው በራሳቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡